EUVIMEDEUVIMED entdecken
Crossref

የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብልሀቶች ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Husien, Abeba, Marew Alemu

National Academic Digital Repository of Ethiopia · 17.02.2023

DOI: 10.20372/ejlcc.v4i1.1415 ↗

Kurz gefasst

Fachartikel in der Zeitschrift National Academic Digital Repository of Ethiopia, erschienen am 17.02.2023. Verfasst von Husien und 2 weiteren Autor:innen.

AbstractBibliografische AngabenZitierenVerwandte Studien

Abstract (Originalsprache)

የጥናቱ ዓላማ የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብለሀቶችን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ የቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ፍትነትመሰል (Quasi- expermental research) ንድፍን መሰረት አድርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በጎንደር ከተማ በልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤት በ2011 ዓ.ም በሰባተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከሚማሩ አምስት ክፍሎች መካከል ከሁለት የመማሪያ ክፍሎች በተራ ዕጣ ናሙና ዘዴ የተመረጡ 120 (60 የሙከራና 60 የቁጥጥር ቡድን) ተማሪዎች ናቸው፡፡ በአንብቦ መረዳትና በማንበብ ግለብቃት እምነት የጽሐፍ መጠይቅ የተሰበሰቡት መረጃዎች በገላጭ ስትስቲክስ፣ በልይይት ትንተና (ANOVA) እና በአበር ልይይት ትንተና (ANCOVA) ተተንትነዋል፡፡ በዚህም በድህረትምህርት አንብቦ የመረዳት ችሎታና በማንበብ ግለብቃት እምነት ውጤት የሙከራው ቡድን በስታትስቲክስ ጉልህ የሆነ የመሻሻል ልዩነት አሳይቷል፡፡ ይህም የተሻጋሪ ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ግለብቃት እምነት የማጎልበት ሚና እንዳላቸው አመላክቷል፡፡ ቁልፍ ቃላት፤ ተሻጋሪ ብልሃት፣ የማንበብ ግለብቃት እምነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ

Zitieren

APA

Husien, Abeba, & Alemu, M. (2023). የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብልሀቶች ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት. National Academic Digital Repository of Ethiopia. https://doi.org/10.20372/ejlcc.v4i1.1415

Vancouver

Husien, Abeba, Alemu M. የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብልሀቶች ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት. National Academic Digital Repository of Ethiopia. 2023. doi:10.20372/ejlcc.v4i1.1415

BibTeX
@article{Husien2023,
  author = {Husien and Abeba and Alemu, Marew},
  title = {የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብልሀቶች ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት},
  journal = {National Academic Digital Repository of Ethiopia},
  year = {2023},
  doi = {10.20372/ejlcc.v4i1.1415}
}
Kostenlos starten →