EUVIMEDEUVIMED entdecken
Crossref

የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች (Graphic organizers) አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን ለማጎልበት ያላቸው ሚና፤

Safisa, Selamawit, Marew Alemu, Mulugeta Teka

National Academic Digital Repository of Ethiopia · 17.02.2023

DOI: 10.20372/ejlcc.v4i2.1410 ↗

Kurz gefasst

Fachartikel in der Zeitschrift National Academic Digital Repository of Ethiopia, erschienen am 17.02.2023. Verfasst von Safisa und 3 weiteren Autor:innen.

AbstractSchlagwörterBibliografische AngabenZitierenVerwandte Studien

Abstract (Originalsprache)

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን በማጎልበት ረገድ ያላቸውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ፍትነትመሰል ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በዶናበርበር የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤት ትምህርታቸውን ከሚማሩ የሰባተኛ ክፍል አምስት ክፍሎች መካከል ከሁለት የመማሪያ ክፍሎች በተራ የዕጣ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 114 (58 የፍትነቱና 56 የቁጥጥሩ ቡድን) ተማሪዎች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ በአንብቦ መረዳት ፈተናና በማንበብ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ በቅድመትምህርትና በድኅረትምህርት ከተሰበሰቡ በኋላ በየዓይነታቸው ተደራጅተው በገላጭ ስታቲስቲክስና በልይይት ትንተና (ANOVA) እንዲሁም የቤንፌሮኒ የጉልህነት ማስተካከያ ስሌትን (p = .025) መሰረት በማድረግ በባለብዙ ልይይት ትንተና (MANOVA) ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ ውጤቱም በቅድመትምህርት ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡት የፍትነቱና የቁጥጥሩ ቡድኖች በድኅረትምህርት የአንብቦ የመረዳት ፈተና (p = .001, partial η2 = .128) በድህረትምህርት የማንበብ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ (p = .001, partial η2 = .116) የፍትነቱ ቡድን ተሳታፊዎች ከቁጥጥሩ ቡድን ተሳታፊዎች በስታቲስቲክስ ጉልህ የሆነ የመሻሻል ልዩነት አሳይተዋል፡፡ ይህ ውጤትም የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት በማጎልበት ረገድ ጉልህ ሚና እንዳላቸው አመላክቷል፡፡ ቁልፍ ቃላት፡- የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች፣ አንብቦ የመረዳት ችሎታ፣ የማንበብ ተነሳሽነት

Schlagwörter

graphic organizerscritical thinkinganalytical thinkinghigh school studentsacademic performancescience educationEnglish language teachingstudent self-disciplinestudent self-regulationstudent self-efficacy

Zitieren

APA

Safisa, Selamawit, Alemu, M., & Teka, M. (2023). የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች (Graphic organizers) አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን ለማጎልበት ያላቸው ሚና፤. National Academic Digital Repository of Ethiopia. https://doi.org/10.20372/ejlcc.v4i2.1410

Vancouver

Safisa, Selamawit, Alemu M, Teka M. የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች (Graphic organizers) አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን ለማጎልበት ያላቸው ሚና፤. National Academic Digital Repository of Ethiopia. 2023. doi:10.20372/ejlcc.v4i2.1410

BibTeX
@article{Safisa2023,
  author = {Safisa and Selamawit and Alemu, Marew and Teka, Mulugeta},
  title = {የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች (Graphic organizers) አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን ለማጎልበት ያላቸው ሚና፤},
  journal = {National Academic Digital Repository of Ethiopia},
  year = {2023},
  doi = {10.20372/ejlcc.v4i2.1410}
}
Kostenlos starten →