EUVIMEDEUVIMED entdecken
Crossref

ተለዋዋጭ ምዘና በአማርኛ አንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለው አስተዋጾ

Tarekegn Tefera, Marew Alemu, Gidey, Tilahun

National Academic Digital Repository of Ethiopia · 21.04.2023

DOI: 10.20372/ejlcc.v5i1.1497 ↗

Kurz gefasst

Fachartikel in der Zeitschrift National Academic Digital Repository of Ethiopia, erschienen am 21.04.2023. Verfasst von Tarekegn Tefera und 3 weiteren Autor:innen.

AbstractBibliografische AngabenZitierenVerwandte Studien

Abstract (Originalsprache)

የዚህ ጥናት ዓላማ ተለዋዋጭ ምዘና በአማርኛ አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለውን አስተዋጾ መመርመር ነበር፡፡ ጥናቱ የተተገበረው በፍትነትመሰል ምርምር ስልት የቅድመና ድኅረትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ንድፍ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም. በባሕርዳር እውቀትፋና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት በሁለት የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ይማሩ የነበሩ 88 የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በምርምሩ የተዘጋጀውን ትምህርት ለስድስት ሳምንታት (12 ክፍል ጊዜያት) ተከታትለዋል፡፡ የአንብቦ መረዳት ትምህርቱን፣ የፍትነት ቡድን ተማሪዎቹ በተለዋዋጭ ምዘና አቀራረብ የተማሩ ሲሆን፣ የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎቹ ደግሞ በመምህርና በተማሪ መጻሕፈት አቀራረብ መሰረት በተለመደው መንገድ ተከታትለዋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች ከምርምሩ በፊትና በኋላ ያሏቸው የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት በፈተናና በጽሑፍ መጠይቅ ተለክቷል፡፡ የተገኙት መረጃዎችም በካይ-ካሬ፣ በነጻ ናሙና ልይይት ትንተናና በመዋቅራዊ እኩልሽ ሞዴል ተፈትሸዋል፡፡ በትንተና ውጤቱ መሰረት የማንበብ ትምህርትን በተለዋዋጭ ምዘና ማስተማር በተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ (β = .386, p = .018) እና የማንበብ ተነሳሽነት (β = .717, p < .001) ላይ ቀጥተኛ አስተዋጾ አለው፡፡ ስለዚህ ተለዋዋጭ ምዘና በመደበኛ ትምህርት ውስጥ በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ መረዳትን ለማስተማር ተግባራዊ ቢደረግ የትምህርት ጥራት ጉድለትን ለማሻሻል አስተዋጾ ይኖረዋል፡፡

Zitieren

APA

Tefera, T., Alemu, M., Gidey, & Tilahun (2023). ተለዋዋጭ ምዘና በአማርኛ አንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለው አስተዋጾ. National Academic Digital Repository of Ethiopia. https://doi.org/10.20372/ejlcc.v5i1.1497

Vancouver

Tefera T, Alemu M, Gidey, Tilahun. ተለዋዋጭ ምዘና በአማርኛ አንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለው አስተዋጾ. National Academic Digital Repository of Ethiopia. 2023. doi:10.20372/ejlcc.v5i1.1497

BibTeX
@article{Tefera2023,
  author = {Tefera, Tarekegn and Alemu, Marew and Gidey and Tilahun},
  title = {ተለዋዋጭ ምዘና በአማርኛ አንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለው አስተዋጾ},
  journal = {National Academic Digital Repository of Ethiopia},
  year = {2023},
  doi = {10.20372/ejlcc.v5i1.1497}
}
Kostenlos starten →